|
English
የቤተ ጉራጌ ባህል ማዕከል (ቤጉባማ)
መግቢያ
የጉራጌ ሕዝብ
በባህል ልማት ለመደራጀት ያደረገው እረጅም ጥረት ሳይዘነጋ የማህበረሰቡ አባላት ህዳር 8 ቀን 1994 ዓ.ም. ምሽት
በግሎባል ሆቴል ያካሄዱት ጉባኤ የሚታወስ ነው።
ከጉባኤው በኋላ
በተነደፈው የማዕከል ማቋቋም መርህ፤
-
ቤተ ጉራጌን
በአንድ ማዕከል በማስተባበር ለዘለዓለም በአንድነት ፀንቶ እንዲኖር ማድረግ ለባህልና ለልማት ዕድገት መሠረት መሆኑን
በመገንዘብ፤
-
ለአስተማማኝና ዘላቂ የባህልና ልማት ዕድገት የሶስትዮሽ የሕዝብ፤ የመንግስት፤ የሕዝባዊ ድርጅት፣ ወዘተ ጥረት ወሳኝነትን
በመቀበል፤
-
በጥሪት፤
በንብረት፤ በዕውቀት፣ በጊዜና በክህሎት፤ በአግባቡና በቁጠባ የመጠቀም ባህልን ማዳበር ለአስተማማኝ ዘላቂ ዕድገት መሠረት
መሆኑን በማመን፤
-
በመግባባት፤
በመደማመጥ፤ በመተማመንና በመከባበር ባህል ላይ የሚገነባ አንድነት ዘላቂነትን በመገንዘብ፤
-
የአገልግሎትና የምርት ግንባታዎች በሚዛናዊነት መጓዝ ውል ላለው የባህል ልማት ዕድገት የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን በማወቅ፤
-
ውስንነቶችንና ስጋቶችን በስልት ተቋቁሞ በጥንካሬዎችና በምቹ ሁኔታዎች፤ በብልሃት ተጠቅሞ የቤተ ጉራጌን ራዕይና
ተልእኮውን እውን ለማድረግ የሚያስችል ውል ያለው የባህል ልማት ማዕከል መፍጠር ወሳኝነትን በማመን፤
-
የሴቶችን
ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማጐልበት የተሟላ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ በመገንዘብ፤
-
ኤች.አይ.ቪ
ኤድስን መዋጋትና ሌሎች ተዛማች በሽታዎችን፣ ብሎም ስብእናው የተሟላና ጤናማ ዜጋ ለማፍራት የወል ጥረት ወሳኝነትን
በመረዳት፤
-
ወጣቱ
ትውልድ አካባቢውን በሁሉም ዘርፍ በባለቤትነት የሚገነባ ኃይል የሚሆንበትን ስልት መቀየስ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፤
የሕዝብ የባህል ልማት
ግንባታ ጥረቶችን ለማገዝ፤ ለማስተባበር፤ ለማደፋፈር፤ ለማነቃቃት፤ ለማጐልበት፤ ለማደራጀትና ለማቀናጀት በማሰብ በኢትዮጵያ
የፍትሐ ብሔር ሕግ መሠረት የቤተ ጉራጌ የባህል ማዕከል እንዲቋቋም ታቅዷል።
ራዕይ
ቤጉባማ
በማያቋርጠው የዓለም የለውጥ ሂደት ውስጥ በአመርቂ የባህል ልማት እድገት አማካኝነት የቤተ ጉራጌን ህዝብ ባህላዊ፣
ሥነልቦናዊና ልማታዊ ፍላጎቶችን በሚዛናዊነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረው ማየት።
ተልዕኮ
-
በራዕዩ
መሠረት መጭውን ዘመን በማገናዘብና ዝግጅት በማድረግ የተባበረና የተቀናጀ ከፍተኛ ባህላዊ እድገት ያለው የቤተ ጉራጌን
ሕዝብ ለማደራጀት የሚያስችል መሠረት መጣል፤
-
በመንግሥት፤
በሕዝብና በሌሎች በሚመለከታቸው ባለጉዳዮች ሁሉ ተሳትፎ የቤተ-ጉራጌ ሕዝብ ባህሉንና አካባቢውን ለማልማት አቅም አጎናጻፊ
ሁኔታ በመፍጠር የህብረተሰቡን ኑሮና ውስጣዊ ግንኙነት የማሳደግ ችሎታ ያላቸውና ስብዕናቸው የተሟላ ግለሰቦች ማፍራት፤
-
የቤተ ጉራጌ
መሬትና ማንኛውንም የተፈጥሮ ሀብት የመንከባከብና የማዳበር አቅም እንዲኖረው ማድረግ፤
ግቦች
-
ቤተ ጉራጌን
በማሰባሰብ ለዘለቄታው ጸንቶ የሚኖር አንድነትና እድገት እንዲኖር ለማድረግ በእውቀት ምንጭነትና አመቻችነት የሚያገለግል
ሁለገብ የባህል ልማት ማዕከል መፍጠር፤
-
የልማት
ተዋናዮችን ሁሉ ባሳተፈ መልኩ የህዝብን የተፈጥሮ ችሎታ፣ አቅምና ልምድ በማቀናጀት ባህሉ፤ ቋንቋው፤ ቅርሱ፤ ታሪኩና
ሁለገብ አካባቢያዊ ልማቱ በአግባቡ እንዲካሄድ፤ እንዲዳብርና እንዲጠበቅ ማገዝ፤
-
በሁሉም
ተሳትፎ የተመሠረተ የባህል ልማትና ራስን በመቻል ጥረት አማካኝነት በውድድር ዓለም የጉራጌ ሕዝብ በብቃት እንዲወጣ
በጥናትና ምክር መደገፍ፤
-
ክስተቶችን
በመተንበይና ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንጂ በሁኔታዎች ሳይዋከብ በአቋም ላይ ተመስርቶ እርምጃ የሚወስድ
(Proactive)
ህብረተሰብ የሚፈጠርበትን ሁኔታ
ማመቻቸት፤
-
ትላልቅ
ከተሞች በሚፈጥሯቸው ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በስልታዊ ሁኔታ ተፈላጊነት ባላቸው ክህሎቶች
እንዲሰለጥኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
-
በአቀማመጥ
በኢትዮጵያ ማዕከልነቱ ሳቢያ የቤተ ጉራጌን ክልል የኢንዱስትሪ ውጤቶችና አገልግሎቶች ማምረቻና ማከፋፈያ እምብርት
እንዲሆን የህዝቡ የሥራ ባህል እንዲዳብር የጥናት፣ የሥርፀትና የምክር አገልግሎት መስጠት፤
እምነቶች
(Values)
-
የቤተ
ጉራጌን አንድነት አጐልማሽ ባህል መገንባትና በአሠራር ዲሞክራሲያዊ ባህልን ማስፈን፤
-
ግልጽነት፣
ተጠያቂነትና ሁሉ አቀፍነትን በመርሕነት ማራመድ፤
-
በመደማመጥ፣
በመተማመንና በመከባበር መጓዝ፣ ግቦች ላይ ለመድረስ ሰላማዊ መንገዶችን መከተል፤
-
ተግባርን
በሕዝብ እመኔታ ማዕከልነትና ተሳትፎ ላይ መመሥረት፤
-
ለገንቢ
ለውጥ ቀና አመለካከት ማሳየትና መዘጋጀት፣ ችግሮችን ለመፍታት በአቋም ላይ የተመሠረተ እርምጃ መውሰድ፤
-
በእኩልነት
ላይ የተመሠረተ ጉድኝት፣ የግንኙነት አውታርና የልምድ ልውውጥ ማካሄድ፤
-
አካባቢን
ተንከባካቢና በእውቀት ላይ የተመሠረተ መዋዕለ ነዋይ የሚያውል ባህል መገንባት።
ዓላማ
ማዕከሉ
በተለያዩ ጥናቶች፣ ስርጸቶችና ምርምሮች አማካይነት፣
-
የጉራጌ
ሕዝብ የተፈጥሮ ችሎታ፣ በጐ ባህል፣ የመደራጀት አቅም፤ የመስራት ፍላጐት፣ የማወቅ ጉጉትና ሌሎችም በጐ አቅሞችን
በማስተባበርና በማዋሐድ የዳበረና የሰከነ ህብረተሰብ መገንባት የሚችልበትን፤
-
በአገርና
አለም አቀፍ ግንባታ ሒደት ውስጥ በአንድ ፊት ተደጋጋፊ ሆኖ በሌላ ፊት ግን ራሱን የቻለ ባህላዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
የጉራጌ አካባቢ የሚመሠረትበትን፤
-
የጉራጌ
አካባቢ የግንቢ ባህል፣ የዕውቀት፣ የካፒታልና የልማት ማዕከል እንዲሆን ሁሉ አቀፍ ጥረትና ልማታዊ ተከታታይ ዝግጅት
የሚደረግበትን፣
-
በቤተሰብ፣
በሕብረተሰብ፣ በሥነ ምግባር፣ በልማድ፣ በባህል፣ በእውቀት፣ ወዘተ ትስሰር የተጠናከረና የተረጋጋ ህብረተሰብ
የሚገነባበትን፤
-
ከጐሰኝነት፣
ከዘረኝነት፣ ከጠባብነት፣ ከትምክህተኝነትና ከዝቅተኛነት ስነልቦና የጸዳ፣ በራሱ የሚተማመንና ከማንም ጋር አብሮ ለመኖር
የሕሊና ዝግጅት ያለው ማህበረሰብ የሚመሠረትበትን፣
-
የሴቶችን
ሁለተናዊ ተሳትፎ በማጐልበት የተሟላ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
-
ኤድስንና
ሌሎች ተዛማች በሽታዎችን በመከላከልና ድህነትን በመቀነስ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የጉራጌን ሕዝብ በጐ ባህላዊና
ማህበራዊ አቅሞች በማስተባበር ኤድስን ለመመከትና ህብረተሰቡን ለመታገድ የሚቻልበትን የምርምር እና የምክር እገልግሎት
የሚሰጥበትን፣
-
ወጣቱ
ትውልድ በባህልና በልማት ፕሮግራም ቀጥተኛ ተሳታፊ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
-
የገጠሩን
ህብረተሰብ የኢኮኖሚ ባህል ደረጃ በደረጃ ወደ አግሮ ኢንዱስትሪ ባህል በማሸጋገር ሥራ መፍጠርና የከተሞች ፈጣን እድገት
በጉራጌ አካባቢ የሚመጣበትን፣
-
ጠቃሚ
ባህላዊ ስርፅቶች ተገቢ እንክብካቤና ጥበቃ የሚያገኙበትን፣
-
በመጨረሻም
የጉራጌ የባህል ማዕከልን በጥናትና ምርመራ ማዕከልነት፣ በልማት ምክርቤትነት፣ በባህላዊ ፍትህና እርቅ ማዕከልነት፣
በአማካሪ ጽ/ቤትነት፣ በአዳዲስ አቅጣጫዎች ቀያሽነት፣ በጥናታዊ ወጐች መዘከሪያነት፤ በኮነፈረንስ ማዕከልነት
የሚያገለግልበትንና የሚደራጅበትን ወዘተ ስልት መጠቆምና ማመቻቸት በዋና ዋናነት የሚጠቀሱ መሠረታዊ መርሆዎች ናቸው።
የቤተ ጉራጌ አንድነት
ይጠንክር!
ኢትዮጵያ በነፃነቷ ለዘለዓለም ትኑር!!!
|